የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ዓርብ መስከረም 29 በሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል። መብራት ኃይል ከአዳማ ከተማ፣ ሀላባ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ የአዲሱን የውድድር ዘመን መጋረጃ ይከፍታል።

በዘንድሮው የውድድር ዘመን 18 ክለቦች የሚሳተፉ ሲሆን፣ ከባለፈው ዓመት የቡድን ክፍፍል ዉድድር ወደ ረደሶ መልስ የውድድሩ ይዘት መመለሱ አንዱ ትልቅ ለውጥ ነው።

መብራት ኃይል ከአዳማ ከተማ

የውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ጨዋታ መብራት ኃይልን ከአዳማ ከተማ ያገናኛል። ሁለቱም ቡድኖች አዲሱን የውድድር ዘመን በድል መጀመር የሚፈልጉ ቢሆንም፣ ለድል የሚያበቃቸው የጨዋታ አቀራረብ ምን ሊመስል ይችላን የሚለዉን እንቃኛልን።

መብራት ኃይል በመጀመሪያው ጨዋታ የተደራጀ የቡድን አቀራረብ ማሳየት ይኖርበታል። በተለይ በመሃል ሜዳ የኳስ ቁጥጥርን መያዝና ከመከላከል ወደ ማጥቃት በፍጥነት መሸጋገር ለቡድኑ ጠቃሚ ይሆናል።

በአዲሱ የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ጨዋታ የተጫዋቾች የጨዋታ ቅንጅት ሙሉ በሙሉ የተሳካ ላይሆን ይችላል። ስለዚህ መብራት ኃይል በተለይ ኳስ በሚያጣበት ጊዜ የመከላከል አደረጃጀቱን መጠበቅ አለበት።

በማጥቃቱ በኩል ደግሞ ከመስመሮች የሚፈጠሩ እድሎችን መጠቀምና በተጋጣሚ የቅጣት ክልል ውስጥ ውጤታማ መሆን ሦስት ነጥብ ለማግኘት ቁልፍ ሊሆን ይችላል።

ለአዳማ ከተማ የመጀመሪያው ፈተና በተጋጣሚው የጨዋታ ፕላን ከመመራት ይልቅ የራሱን የጨዋታ ሂደት መቆጣጠር ነው።

ቡድኑ በመሃል ሜዳ የተጫዋቾችን ቁጥር በማብዛት የተጋጣሚውን የኳስ ስርጭት ማስተጓጎል እና ኳስ ሲያገኝ በፍጥነት ወደ ፊት መንቀሳቀስ ይኖርበታል። በተለይ በተጋጣሚው የመከላከል መስመር ጀርባ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን መጠቀም የአዳማ ከተማ የማጥቃት እቅድ አካል ሊሆን ይችላል። ሆኖም ቡድኑ በማጥቃት ላይ ከመጠን በላይ ተጠምዶ የመከላከል ክፍተት እንዳይፈጥር መጠንቀቅ ይኖርበታል።

የጨዋታው ቁልፍ ጉዳይ በመሃል ሜዳ የሚኖረው ፉክክርና ሁለቱ ቡድኖች የሚፈጥሯቸውን የግብ እድሎች ወደ ግብ የመቀየር ብቃት ይሆናል።

ሀላባ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ

ሁለተኛው የመክፈቻ ቀን ጨዋታ ሀላባ ከተማን ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያገናኛል።

ይህ ጨዋታ በተለይ ለሀላባ ከተማ በከፍተኛው ሊግ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማሳየት በደጋፊው ፊት የመጀመሪያ ጨዋታዉን ማድረጉ ትልቅ እድል ነው። በሌላ በኩል ወልዋሎ በአህጉራዊ ውድድር ያገኘውን የጨዋታ ልምድ በሀገር ውስጥ ውድድር ላይ ለመጠቀም ጥሩ አጋጣሚ ነው።

ሀላባ ከተማ በመጀመሪያው ጨዋታ በተለይ የመከላከል ተግባቦቱን ማጠናከር ይኖርበታል። አዲስ የውድድር ዘመንን በድል ለመጀመር ያለው ፍላጎት ቡድኑ ያለ እቅድ ማጥቃት ላይ ብቻ ማተኮር የለበትም። የወልዋሎን የማጥቃት እንቅስቃሴ በመገደብ እና ኳስ በሚያገኝበት ጊዜ ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እድሎችን በመፍጠር ተጋጣሚውን ማስቸገር ይችላል። በተለይ የቆሙ ኳሶችን በትክክል መጠቀም እና በተጋጣሚው ሶስተኛ የሜዳ ክፍል ውስጥ የሚፈጠሩ ጥቂት እድሎችን ወደ ግብ መቀየር ለሀላባ ከተማ ወሳኝ ይሆናል።

ወልዋሎ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከሊጉ በተጨማሪ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመሳተፍ ኃላፊነት ያለበት ቡድን ነው። በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመራው ቡድን በክረምቱ የዝውውር ወቅት ካርሎስ ዳምጠው፣ በረከት ሳሙኤል፣ እዮብ አለማየሁ እና አህመድ ረሺድን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾችን አስፈርሟል።

ከወልዋሎ የሚጠበቀው ትልቁ ነገር በአህጉራዊ ውድድር ያገኘውን ልምድ በሊጉ ውስጥ ወደ ውጤት መቀየር ነው። በተለይ በተከታታይ ውድድሮች የሚፈጠረውን የተጫዋቾች ድካም ታሳቢ ያደረገ የቡድኑን ጥልቀት በተገቢው መንገድ መጠቀም ይኖርበታል።

ወልዋሎ ከሀላባ ከተማ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የኳስ ቁጥጥርን በመያዝ፣ በመሃል ሜዳ ብልጫ በመውሰድና የተጋጣሚውን የመከላከል መስመር በተደጋጋሚ በመፈተን ሦስቱን ነጥቦች ለማሳካት መጣር አለበት። ሆኖም በአህጉራዊ ውድድር መሳተፉ ብቻ በሊጉ ውስጥ ብልጫ እንደሚኖረው ዋስትና አይሰጥም። በተለይ ከአዲስ ተወዳዳሪ ጋር በሚደረግ ጨዋታ ተጋጣሚን አቅልሎ መመልከት ዋጋ ሊያስከፍልው ይችላል።

የመጀመሪያው ሳምንት ምን ይነግረናል?

የአዲሱ የውድድር ዘመን መክፈቻ ጨዋታዎች የክለቦችን የሙሉ ዓመት አቅም ለመመዘን በቂ ባይሆኑም፣ ስለ ቡድኖቹ የዝግጅት ደረጃ የመጀመሪያ ግንዛቤ ይሰጣሉ። በተለይ በክረምቱ የዝውውር ወቅት የተደረጉ ለውጦች፣ የአዳዲስ ተጫዋቾች ቅንጅት፣ የአሰልጣኞች የጨዋታ አቀራረብ እና የቡድኖች አካላዊ ዝግጁነት በመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች የሚፈተኑ ጉዳዮች ናቸው።

ለአራቱም ቡድኖች የመጀመሪያውን ሦስት ነጥብ ማግኘት በሊጉ ሰንጠረዥ ላይ ጥሩ ጅማሮ ከማድረግ ባሻገር ለቀጣይ ጨዋታዎች የሚያስፈልገውን የስነ-ልቦና ጥንካሬ ይሰጣል።

የFootball Ethiopia ዳሰሳ