የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ የቁልቁለት ጉዞ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ የቁልቁለት ጉዞ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለፉት ቅርብ ወራቶች ያስመዘገባቸው ዓለም አቀፍ ውጤቶች ከአንድ ቡድን ወይም ከአንድ አሰልጣኝ አቅም በላይ የሆነ ጥያቄ ያስነሳሉ። ከዋናው የወንዶች ብሔራዊ ቡድን እስከ ወጣት ቡድኖች፣ ከሴቶች ብሔራዊ ቡድን እስከ አገሪቱን በአፍሪካ የክለቦች ውድድር የወከሉት ክለቦች ድረስ የታዩት ውጤቶች፣ የእግር ኳሳችን ደረጃ የት እንደሚገኝና ወደየት እያመራ እንደሆነ በጥልቀት እንድንመለከት ያስገድዳል።

ቡና በሜዳው ለሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታ ተሸነፈ

ቡና በሜዳው ለሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታ ተሸነፈ

ኢትዮጵያ ቡና በሜዳው ኢትዮ ኤሌክትሪክን አስተናግዶ 1 ለ 0 በመሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታ በደጋፊዎቹ ፊት ነጥብ ጣለ። በአዲሱ አሰልጣኝና በአዲስ በተዋቀረው ቡድን ላይ ከፍተኛ ተስፋ የጣሉት የቡና ደጋፊዎችም በሜዳቸው ሌላ አሳዛኝ ውጤት ለማስተናገድ ተገደዋል።

መሳይ ተፈሪ የ10 ጨዋታዎች እገዳና የ10 ሺህ ብር ቅጣት ተጣለባቸው

መሳይ ተፈሪ የ10 ጨዋታዎች እገዳና የ10 ሺህ ብር ቅጣት ተጣለባቸው

የወላይታ ድቻ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ፣ ቡድናቸው ከባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የሦስተኛ ሳምንት ጨዋታ በፈጸሟቸው የዲሲፕሊን ጉድለቶች በድምሩ ከ10 ጨዋታዎች እንዲታገዱና 10 ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው። ሐሙስ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ከባሕር ዳር ቡድን ጋር በተደረገው ጨዋታ በ90+4ኛው ደቂቃ ዳኞችን በአጸያፊ ቃላት በመሳደባቸው በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግደዋል። ለዚህ ጥፋት የስድስት ጨዋታዎች እገዳና የአምስት ሺህ ብር መቀጮ ተጥሎባቸዋል።

የጊዮርጊስ 3 ነጥብ ፍለጋ ሲቀጥል፤ ባንክ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጥዋል

የጊዮርጊስ 3 ነጥብ ፍለጋ ሲቀጥል፤ ባንክ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጥዋል

በአሰልጣኝ ሚቾ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስብስብ፣ በሦስተኛው የሊግ ጨዋታውም ሙሉ ሦስት ነጥብ ማግኘት አልቻለም። በአዲስ አበባ ስታዲየም ከአዳማ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ፣ ቀድሞ ግብ ተቆጥሮበት ከኋላ በመነሣት 1–1 ተለያይቷል። አዳማ ከተማ በ10ኛው ደቂቃ ቢንያም አይተን ባስቆጠረው ግብ መሪነቱን ይዟል። ሆኖም ግቡ ከጨዋታ ውጭ ከሚመስል አቋቋም በተነሣ እንቅስቃሴ መገኘቱ አከራካሪ ነበር። ጊዮርጊስ አቻ ለመሆን ሲታገል ቆይቶ፣ በ63ኛው ደቂቃ አብዱልሀሚድ ሙባረክ ባስቆጠረው የጭንቅላት ግብ ወደ ጨዋታው ተመልሷል። የአቻነት ግቡ የተገኘበት የማዕዘን ምት ውሳኔም እንዲሁ ጥያቄ የተነሣበት ነበር። የዋና ዳኛውና በተለይ የረዳት ዳኞቹ ውሳኔዎች በጨዋታው ሂደት ላይ ጥላ አጥልተዋል። በሁለቱም ግቦች አመጣጥ የታዩት የተሳሳቱ ውሳኔዎች፣ ሁለቱንም ቡድኖች በተለያየ ጊዜ ተጠቃሚ አድርጎዋል።

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን፤ አጠያያቂው የአሰልጣኝ ሹመትና የተጫዋቾች ምርጫ

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን፤ አጠያያቂው የአሰልጣኝ ሹመትና የተጫዋቾች ምርጫ

ዳንኤል ፀሐዬ በቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ዘመን ረዳት አሰልጣኝ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። በወቅቱ በእግር ኳስ አመራር ውስጥ የፖለቲካ ተጽዕኖና የግል ትውውቅ በሹመቶች ላይ ሚና እንዳላቸው ትችቶች ይነሱ ነበር። ይሁን እንጂ የዳንኤል ሹመት በፖለቲካዊ ትስስር የተፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳይኖር እንደ እውነታ መቅረብ አይገባውም። ሆኖም በወቅቱ ከእሳቸው የበለጠ የስልጠና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች እያሉ ለዚያ ኃላፊነት መመረጣቸው አጠያያቂ ነበር። አሁንም በክለብ ደረጃ የተሻለ ውጤት ያሳዩ አሰልጣኞች እያሉ ሌላ የብሔራዊ ቡድን ኃላፊነት ማግኘታቸው ግልጽ ማብራሪያ የሚፈልግ ጉዳይ ነው።

የዜና ማህደር

ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ የ2019 ሊግ የግብ ክብረ ወሰን ያስመዘገበበት ጨዋታበሦስተኛው ሳምንት የኢትዮጲያ ፕርሚዬር ሊግ መክፈቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድል ሲቀናው፣ ሀላባ ከተማና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ«የምሥራቅ አፍሪካ እግር ኳስ ያልተጠቀመበት የወርቅ ማዕድን ነው፤ ኢትዮጵያውያንም ትዕግሥት ሊያደርጉ ይገባል» ቤንጃሚን ዚመርማንየመጨረሻ ደቂቃዎች ድራማ በሆሳዕና ከተማ፣ ታሪካዊ ድል ለንግድ ባንክኢትዮጵያ ቡና የሸገር ደርቢን አሸነፈ፤ ሀዋሳ ከተማና መድን ነጥብ ተጋርተዋልሀላባ ከተማ በታሪኩ የመጀመሪያዉን የፕርሚዬር ሊግ ጨዋታ አሸነፈ፤ የሁለተኛው ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ዉሎዎችወኔ የተሞላበት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቃለ ምልልስ፦ «ኢትዮጵያውያን አምበሶች ናቸው!»ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ አቻ ተለያይታ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፈች፤ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን ለማረጋገጥም ሁለት ዕድሎች አሏትየኢትዮጵያ የሴቶች ኦሎምፒክ ቡድን ሩዋንዳን በድምር ውጤት 2 ለ 1 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈኢትዮጵያ ቡሩንዲን በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ የማለፍ ተስፋዋን አጠናከረችሁሉም ባለ ሜዳ ክለቦች ነጥብ የጣሉበት የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎችቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ የውድድር ዓመቱን በአቻ ውጤት ጀመሩ