የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞውን በሱዳን 1-0 በመሸነፍ ጀምሯል።

በምድብ 10 የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ሱዳን እና ኢትዮጵያ ዓርብ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. በደቡብ ሱዳን ጁባ ብሔራዊ ስታዲየም ተገናኝተዋል።

ጨዋታው ለረጅም ደቂቃዎች ያለ ግብ 0-0 የቀጠለ ሲሆን፣ የጨዋታው ወሳኝ ክስተት በ86ኛው ደቂቃ ተከስቷል። ሱዳን ያገኘችውን የፍጹም ቅጣት ምት መሐመድ ማሙን ኢሳ ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን 1-0 መሪ አድርጓል።

ኢትዮጵያ በቀሪዎቹ ደቂቃዎች የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ብትሞክርም ሳይሳካላት ቀርቶ፣ ሱዳን ጨዋታውን 1-0 በማሸነፍ ሦስት ነጥብ ይዛ ወጥታለች።

የምድብ 10 ቀጣይ ጨዋታዎች

በዚህ ውጤት ሱዳን ሦስት ነጥብ በማግኘት የማጣሪያ ጉዞዋን በድል ስትጀምር፣ ኢትዮጵያ ያለ ነጥብ የምድቡን ውድድር ጀምራለች።

ሱዳን በቀጣይ ጨዋታዋ ሞዛምቢክን የምትገጥም ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ደግሞ ሴኔጋልን በባህር ዳር ስታዲየም ታስተናግዳለች።

ዋልያዎቹ ከሴኔጋል ጋር በሚያደርጉት ቀጣይ ጨዋታ ከመጀመሪያው ሽንፈት አገግመው የማጣሪያውን የመጀመሪያ ነጥባቸውን ለማግኘት ይጫወታሉ።

የመጨረሻ ውጤት፦ ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያ
ግብ፦ መሐመድ ማሙን ኢሳ 86' (ፍ.ቅ.ም)
ውድድር፦ የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ – ምድብ 10
ስታዲየም፦ ጁባ ብሔራዊ ስታዲየም፣ ጁባ፣ ደቡብ ሱዳን