በ2028 ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን፣ ከሲሸልስ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያደርጋል።

የመጀመሪያው የወዳጅነት ጨዋታ ረቡዕ መስከረም 20 ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል።

ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን በተመሳሳይ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል።

እነዚህ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2028 ኦሊምፒክ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ የሚያደርገው ዝግጅት አካል ናቸው።