የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሴኔጋል ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን በባህር ዳር ከተማ ቀጥሏል።

ዋልያዎቹ በባህር ዳር ብሉ ናይል ሪዞርት ሆቴል ማረፊያቸውን ያደረጉ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም በባህር ዳር ስታዲየም የመጀመሪያ የልምምድ መርሃ ግብራቸውን አከናውነዋል። ቡድኑ ከሴኔጋል ጋር ለሚጠብቀው ወሳኝ ጨዋታ ዝግጅቱን በቀጣዮቹ ቀናት ይቀጥላል።

በሌላ በኩል መስፍን ታፈሰ ከሱዳን ጋር በተደረገው ጨዋታ የማስጠንቀቂያ ካርድ በመመልከቱ፣ በሁለት ቢጫ ካርዶች ቅጣት ምክንያት ከሴኔጋል ጋር ከሚደረገው ጨዋታ ውጪ ሆኗል። የተጫዋቹ አለመኖር የአሰልጣኞቹን የጨዋታ እቅድ ለውጥ እንዲያደርግ የሚያስገድድ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ተጋጣሚ የሆነው የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድንም በዛሬው ምሽት ባህር ዳር ደርሷል። የሴኔጋል ልዑካን ቡድን ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በባህር ዳር ለሚያደርጉት ጨዋታ የመጨረሻ ዝግጅታቸውን በከተማዋ ያከናውናሉ።